Fana: At a Speed of Life!

በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ፋሲል ከነማ የታንዛኒያውን አዛም አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 5፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታ በሜዳው የታንዛኒያው አዛምን ያስተናገደው ፋሲል ከነማ ድል ቀንቶታል።

በዛሬው እለት በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታው ላይ ፋሲል ከነማ የታንዛኒያውን አዛም የእግር ኳስ ክለብን 1ለ0 በሆነ ውጤት ነው መርታት የቻለው።

የፋሲል ከነማን ብቸኛ የማሸነፊያ ጎልም በዛብህ መለዮ በ45ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ይህንን ከተክሎም ፋሲል ከነማ በሜዳው 3 ነጥብ በመያዝ በቀጣይ ከአዛም የእግር ኳስ ክለብ ጋር ለሚኖረው የመልስ ጨዋታ ዝግጅት የሚያደርግ ይሆናል።

ፋሲል ከነማ እና የታንዛኒያው አዛም እግር ኳስ ክለብ የመልስ ጨዋታም ከ15 ቀናት በኋላ በታንዛኒያ ዳሬ ሰላም ከተማ እንደሚካሄድ ነው የሚጠበቀው።

You might also like
Comments
Loading...