Fana: At a Speed of Life!

በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ አህጉራዊ የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ንቅናቄ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 20፣ 2011(ኤፍ ቢ ሲ) በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ አህጉራዊ የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ንቅናቄ በአዲስ አበባ ሊካሄድ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ንቅናቄው ‹‹የአፍሪካ ኢኖቬሽን ሳምንት›› በሚልመሪ ቃል  ከጥቅምት 17 እስከ ጥቅምት 22 ቀን 2012  ዓ.ም ድረስ ነው በአዲስ አበባ ከተማ የሚካሄደው ።

የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ንቅናቄውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአይቢኤ ኢትዮጲያና ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመተባበር የሚዘጋጁት መሆኑ ተገልጿል።

በዚህ መርሃ ግብር ላይም  ችግር ፈቺ፤ ሀብት ፈጣሪና ወደ ምርትና አገልግሎት ሊቀየር የሚችል የፈጠራ ስራ ያላቸው ባለሙዎች በዚህ አህጉራዊ መድረክ ላይ ሀገራችውን መክለው እንዲወዳደሩ ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል።

ይህም  ባለሙያዎች  የፈጠራ ውጤቶቻቸውን  ለውጭና ለሀገር ውስጥ ባለሃብቶች፤ ለቬንቸር ካፒታል ተቋማት እና ለሌሎች የፋይናስ ምንጮች በማስተዋወቅ ወደ ምርትና አገልግሎት እንድትቀላቀሉ የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል።

በውድድሩ ትኩረት  የሚሰጣቸው ዘርፎችም ዘመናዊ ከተሞች እና አዳዲስ የመኖሪያ ቴክኖሎጂዎች፤ ዲጂታላይዜሽን፤ የኢንተርኔት ንግድ ስርዓት፤ የግብርና፤ የጤናና የህክምና ቴክኖሎጂ፤ መስተንግዶና ቱሪዝም፤ የማምረቻና እና የማዕድን ኢንደስትሪ ዘርፎች ናቸው ተብሏል።

መወዳደር የሚፈልጉ የስራ ፈጠራ ባለሙያዎችም የፈጠራ ስራ ፕሮፖዛላቸውን በኢሜይል አድራሻ Registration@africainnovationweek.com ላይ በመላክ መመዝገብ የሚችሉ መሆኑ ተጠቁሟል።

You might also like
Comments
Loading...