Fana: At a Speed of Life!

በመጠጥ ውሃ ውስጥ የሚገኙ ጥቃቅን ፕላስቲኮች አሁን በሚገኙበት ደረጃ ለጤና አያሰጉም-የአለም ጤና ድርጅት

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 16፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመጠጥ ውሃ ውስጥ የሚገኙ ጥቃቅን ፕላስቲኮች (ከ5 ሚሊሜትር መጠን በታች) አሁን በሚገኙበት ደረጃ ለጤና እንደማያሰጉ የአለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡

የአለም ጤና ድርጅት በጉዳዩ ዙሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ ባወጣው ሪፖርት በጣም ዝቅተኛ መጠን ያለው ፕላስቲክ ከሰውነት ጋር ምንም አይነት ንክኪና ግንኙነት ሳይፈጥር እንደሚያልፍ ይፋ አድርጓል፡፡

ሆኖም የአለም ጤና ድርጅት በአስቸኳይ ተጨማሪ ነገሮች ማወቅ ይገባናል ብሏል ባወጣው ሪፖርት፡፡

ዝቅተኛ መጠን ያለው ፕላስቲክ ማለት ከ5 ሚሊ ሜትር መጠን በታች ሲሆን በወንዞች፣ ሀይቆች፣ በመጠጥ ውሃዎች እንዲሁም በታሸጉ ውሃዎች ውስጥ የሚገኝ ነው፡፡

በመሆኑም በዚህ መጠን የሚገኝ የፕላስቲክ በአሁን ወቅት ለጤና ስጋት እንዳማይሆን የተገለፀ ሲሆን ተጨማሪ ምርምሮች ግን ያስፈልጋሉ ተብሏል፡፡

በመጠጥ ውሃ ውስጥ በሚገኝ ፕላስቲክ ላይ የሚደረገው ጥናት ሁለት አስርት ዓመታትን ያስቆጠረ በመሆኑ የአለም ጤና ድርጅት እንደገለፀው የሚገኙ መረጃዎች የተወሰኑ ናቸው ተብሏል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

You might also like
Comments
Loading...