Fana: At a Speed of Life!

2ኛው ዙር የማስ ስፖርት መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለተኛው ዙር የማስ ስፖርት መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ ተካሄደ፡፡

ወርሃዊ በሆነው በዚህ የማስ ስፖርት መርሃ ግብር ላይ የ3 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫን ጨምሮ የተለያዩ ስፖርታዊ ክንውኖች ተካሂደዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ አምባሳደሮች፣ ሚኒስትሮች እና የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን÷ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ከግሪክ እና ጃፓን አምባሳደሮች የኦሎምፒክ አክሊል እና “ማስኮት” ተበርክቶላቸዋል፡፡

በዚሁ ፕሮግራም ላይ የቀድሞ አትሌቶች፣ አርቲስቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና የተለያዩ የስፖርት ማህበራትን ጨምሮ ከ10ሺ በላይ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች መሳተፋቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡

Photo Credit: Mayor Office of Addis Ababa

You might also like
Comments
Loading...