Fana: At a Speed of Life!

ፕሪምየር ሊጉን የተቀላቀለው ወልቂጤ ከተማ አዲስ አሰልጣኝ ቀጠረ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 10፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያን ፕሪምየር ሊግ መቀላቀሉን ያረጋገጠው ወልቂጤ ከተማ የአዲስ አሰልጣኝ አስፈረመ፡፡

የከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ ቻምፒዮን በመሆን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያደገው ወልቂጤ ከተማ ደግአረግ ይግዛውን ለመቅጠር ከስምምነት መድረሱን ነው ያስታወቀው፡፡

አሰልጣኝ ደግአረግ ከዚህ ቀደም በባህር ዳር ከተማ በ2001ዓ.ም ከዛም በባህርዳር ዩንቨርስቲ እና አውስኮድ ከሰሩ በኋላ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በኢኮስኮ ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡

አዲሱ አሰልጣኝ ማረፊያዬን ወልቂጤ ከተማ አድርጌያለሁ ፤ ለምመርጠው አጨዋወት የሚመቹ ነገሮችን ያሟላ ክለብ መሆኑን ተገንዝቤ ቀጣዩን ዓመት አብሬ ለመስራት ወስኛለው ብለዋል፡፡

በዚህም ደስተኛ መሆናቸውን የተናገሩት ደግአረግ ይግዛው በቆይታዬም ከአመራሩ ጋር በመተባበር የሚጠበቅብኝን ለማድረግ ጥረት አደርጋለው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የወልቂጤ ክለብ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አበባው ሰለሞን በበኩላቸው የቀጠርነው አሰልጣኝ በትምህርት ደረጃውም ሆነ በካፍ ላይሰንስ ብቁ ነው ብለዋል።

በወጣቶች ላይ የሚያምን፣ በሰራቸው ቡድኖች ላይ ማራኪ የኳስ ፍሰት የሚያሳይ እና ጠንካራ ቡድን የሚሰራ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፡- ሰኮር ኢትዮጵያ

You might also like
Comments
Loading...