Fana: At a Speed of Life!

ፌስቡክ፣ ኢንስታግራምና ዋትስአፕ የፎቶ እይታ ችግር አጋጠማቸው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  ፌስቡክ፣ ኢንስታግራምና ዋትስአፕ የፎቶ እይታ ችግር ትናት ምሽት አጋጠማቸው፡፡

ምሽቱን ኩባንያው  ሶስቱ መተግበሪያዎቹ ፎቶና ተንቀሳቃሽ ምስል የማሳያት ችግር እንዳጋጠማቸውና  በፍጥነት ለማስተካከል እየሰራ እንደነበረ አስውቋል፡፡

ከቆይታ በኋላ አጋጥሞት የነበረውን ችግር በመቅረፍ ወደ ተለመደ አገልግሎቱ መመለሱን በመግለፅ ለተፈጠረው ችግር ደንበኞቹን ይቅርታ ጠይቋል፡፡

ግዙፉ የማህበራዊ ሚዲያ ኩባንያ ሁለቱ የመልዕክት መለዋወጫ እና የፎቶ ማጋሪያ መተግበሪያው በቢሊየን የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች አሉት፡፡

በተመሳሳይ ትዊተርም  የተወሰኑ ደንበኞቹ መልዕክቶችን በቀጥታ ማስተላለፉ እና መቀበል እንደማይችሉ አሳስቦ እንደነበረ ተነግሯል፡፡

በመጋቢት ፌስቡክና ኢንስታግራም በታሪካቸው ለረጅም ጊዜ የቆየ  ችግር አጋጥሟቸው እንደነበረ የሚታወስ ሲሆን በሚያዚያ ወር እንዲሁ ችግር አጋጥሟቸው ነበር፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

You might also like
Comments
Loading...