Fana: At a Speed of Life!

ጨፌ ኦሮሚያ ከሃምሌ 7 ጀምሮ መደበኛ ጉባኤውን ያካሂዳል

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 5፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጨፌ ኦሮሚያ ከሃምሌ 7 እስከ ሃምሌ 9 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ መደበኛ ጉባኤውን ያካሂዳል፡፡

በጉባኤው በክልሉ የ70 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ረቂቅ በጀት ላይ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሎሚ በዶ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፥ ከመደበኛ ጉባኤው አንድ ቀን ቀደም ብሎ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በተገኙነት 12 ሺህ ችግኞች እንደሚተከሉ ተናግረዋል፡፡

በጉባኤው የ2011 የክልሉ የስራ አፈፃፀም ቀርቦ በጉባኤተኞቹ ውይይት እንደሚደረግበትም ነው አፈ ጉባኤዋ የገለጹት፡፡

የተለያዩ መመሪያዎች እና ደንቦችም ይጸድቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አስረድተዋል።

በተጨማሪም በሀገሪቱ በፖለቲካው መስክ የተገኘውን ድል ወደ ኢኮኖሚው ለማሸጋገር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ አቅጣጫ ማስቀመጥ እና ሹመቶችን መስጠትም ከጉባኤው ይጠበቃል ነው ያሉት።

ጨፌው ባለፈው በጀት አመት 16 የተለያዩ ደንቦች እና መመሪያዎችን በማጽደቅ በተለያዩ አማራጮች ለክልሉ ስራ አስፈፃሚዎች እና ህዝብ እንዲደርስ ማድረጉንም አስረድተዋል፡፡

በአፈወርቅ አለሙ

You might also like
Comments
Loading...