Fana: At a Speed of Life!

ጣፋጭ መጠጦች ለካንሰር አጋላጭ መሆናቸው ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 4 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የፍራፌ ጁስን ጨምሮ ጣፋጭ ወይንም ስኳር ያለባቸውን መጠጦች  መጠቀም የሰዎችን የካንሰር ተጋላጭነት ከፍ እንደሚያደርግ የፈረንሳይ ተመራማሪዎች ይፋ አደረጉ፡፡

በብሪታኒያ የህክምና ጆርናል ላይ የወጣው ይህ አዲስ ጥናት ለአምስት አመታት በ100 ሺህ ሰዎች ላይ ክትትል ማድረጉ ነው የተጠቆመው፡፡

በፓሪስ የሚገኘው የሶርቦኔ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች ጥናት በደም ውስጥ የሚገኘው የስኳር መጠን ለዚህ ችግር ዋነኛ ምክንያት መሆኑን አስፍሯል፡፡

ሆኖም ይህ ጥናት በጉዳዩ ዙሪያ መጨረሻውን  ማረጋገጫ  አይደለም የተባለ ሲሆን ተመራማሪዎቹ ተጨማሪ ጥናቶች እንዲካሄዱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሱኳር ያለበት ወይንም  ጣፋጭ  መጠጥ ማለት ከ5 በመቶ በላይ ስኳር በውስጡ የያዘ እንደሆነ ነው ባለሙያዎች የሚናገሩት፡፡

ይህም ስኳር ያልተጨመረበትን የፍራፍሬ ጁስ፣ ለስላሳ መጠጠቶች፣ ጣፋጭ ወተቶች፣ ሀይል ሰጪ እንዲሁም ስኳር የተጨመረባቸውን ሻይና ቡናዎች የሚያካትት ነው ተብሏል፡፡

በየቀኑ 100 ሚሊ ሌትር ተጨማሪ ጣፋጭ መጠጥ ወይንም በሳምንት ውስጥ ሁለት ኩባይ ጣፋጭ መጠጥ መጠጣት  ሰዎች ለካንሰር ያላቸውን ተጋላጭነት 18 በመቶ ከፍ ያደርገዋል፡፡

በዚህ ጥናት መሰረት 1 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች በ22 የካንሰር አይነቶች ተጋላጭ እንደሚሆኑ የተነገረ ሲሆን ተጨማሪ 100 ሚሊ ሌትር ጣፍጭ መጠጥ የሚጠጡ ከሆነ የካንሰር አይነቱ ወደ 26 ከፍ እንደሚል ተነግሯል፡፡

 

ምንጭ፡- ቢቢሲ

You might also like
Comments
Loading...