Fana: At a Speed of Life!

የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴን መግታትና ህገ ወጥ ንግድን መከላከል የገቢዎች ሚኒስቴር ቀጣይ የትኩርት አቅጣጫ ነው- ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 16፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴን መግታት እና ህገ ወጥ ንግድን መከላከል የገቢዎች ሚኒስቴር የቀጣይ አመት የትኩርት አቅጣጫ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስትር አዳነች አቤቤ ተናገሩ።

የገቢዎች ሚኒስቴር በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ውስጥ የተሻለ የሰሩ ዳይሬክቶሬቶች እና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች በዛሬው እለት እውቅና ሰጥቷል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀት ምስጋና እና እውቅና ዝግጅት ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ እና የገቢዎች ሚኒስትር ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

የገቢዎች ሚኒስትር አዳነች አቤቤ በሚሊንየም አዳራሽ እየተካሄደ ባለው የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች የምስጋናና የእውቅና መድርክ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።

ሚኒስትሯ ባደረጉት ንግግር፥ በ2011 በጀት ዓመት እንደገቢዎች ሚኒስትር በገቢ አሰባሰቡ የተሻለ አፈጻጸም እንዲመዘገብ ሰራተኛው እና አመራሩ በትጋት በመስራታቸው ምስጋና አቅርበዋል።

በዚህም በባለፈው አመት 198 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ገቢን ሚኒስቴሩ ሰብስቧል ይህም ከባለፈው አመት የ22 ቢሊየን ብር ጭማሬ አሳይቷል።

የሚኒስቴሩ ሰራተኞች በቀጣይ ለመሰብሰብ የታቀደውን 248 ቢሊየን ብር ለማሳካት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

በአዳነች አበበ

You might also like
Comments
Loading...