Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻችውን አስመረቁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻችውን አስመረቁ።

ዛሬ ተማሪዎቻቸውን ካስመረቁት ዩኒቨርሲቲዎች መካከልም የሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ ይገኝበታል።

ዩኒቨርሲው በተለያዩ መርሃ ግብር ያስተማራቸውን ከ 5 ሺህ የሚበልጡ ተማሪዎችን አስመርቋል።

በተጨማሪም ለአርቲስት አሊ ሸቦ እና ለዶክተር አበራ ደሬሳ የክብር ዶክተሬት ሰጥቷል።

በሌላ በኩል የጎንደር ዩኒቨርሲቱ በተለያዩ የትምህርት መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን  8 ሺህ 365 ተማሪዎችን  ዛሬ አስመርቋል።

ከተመራቂዎቹ መካከልም 3 ሺህ 227 ተማሪዎች ሴቶች ናቸው።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአፋር ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ አወል አርባ ተመራቂዎች በራሳቸው አቅምና ሀይል በመተማመን የጋራ ሀገራቸውን እንዲገነቡ ጥሪ አቅርበዋል።

ዩኒቨርሲቲው በአሁኑ ወቅት 47 ሺህ 723 ተማሪዎችን በማስተማር ላይ እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አስራት አፀደ ወይን መናገራቸውን ባለድረባችን አገኘው አበባው ከስፍራው ዘግቧል።

በሌላ በኩል የወልዲያ ዩኒቨርሲቱ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ድግሪ መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 627 ተማሪዎችን አስመርቋል።

በተጨማሪም ጅማ፣ ወለቂጤ፣ ደብረ ታቦር እና ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን አስመርቀዋል።

You might also like
Comments
Loading...