Fana: At a Speed of Life!

የብሪታኒያ አየር መንገድ ወደ ካይሮ የሚያደርገውን በረራ አቋረጠ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ14፣ 2011(ኤፍ ቢ ሲ) የብሪታኒያ አየር መንገድ ወደ ግብፅ ካይሮ የሚያደርገውን የበረራ አገልግሎት ለአንድ ሳምት ያክል ጊዜ ማቋረጡን አስታውቋል።

አየር መንገዱ በረራውን ያቋረጠውም በሀገሪቱ የደህንነት ስጋት መኖሩን ተከትሎ ነው ተብሏል።

ይሁን እንጂ አየር መንገዱ በረራውን ለማቋረጥ ያስገደደውን የደህንነት ስጋት ምንነት ዝርዝር ከመግለፅ ተቆጥቧል።

የብሪታኒያ አየር መንገድ ቃል አቀባይ  ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ አየር መንገዱ ወደ ካይሮ ለሚያደርገው በራራ ባደረገው ቅድመ  ምርመራ የደህንነት ችግር መኖሩን አረጋግጧል ብለዋል።

ስለሆነም አየር መንገዱ  ለደንበኞች እና ሰራተኞች ደህንነት ሲባልና ችግሩን በጥልቀት ለመመርመር  ወደ ግብፅ የሚያደርገውን የበረራ አገልግሎት ለሰባት ቀናት  ማቋረጡን ተናግረዋል።

የካይሮ አየር ማረፊያ ቃል አቀባይ  በበኩላቸው ጉዳዩን አስመልክቶ የብሪታንያ አየር መንገድ  ማብራሪያ እንዲሰጣቸውም መጠየቃቸውን ጠቁመዋል።

በተመሳሳይ ባለቤትነቱ የጀርመን አየር መንገድ  የሆነው ሉፍታንዛ  በትናንትናው ዕለት ወደ ካይሮ የሚያደርገውን በረራ መሰረዙን አስታውቆ ነበር ።

ይሁን እንጂ እንዲቋረጥ ተደርጎ የነበረው  በረራ በዛሬው ዕለት እንዲቀጥል መደረጉን የአየር መንገዱ ቃል አቀባይ አስታውቀዋል ።

ምንጭ ፥ቢቢሲ

 

You might also like
Comments
Loading...