Fana: At a Speed of Life!

ዋትስአፕ በኮምፒውተር ላይ የሚሰራ መተግበሪያ እየሰራ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 24፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የመልእክት መለዋወጫ መተግበሪያ የሆነው ዋትስአፕ ከስማርት ስልክ በተጨማሪ ኮምፒውተር ላይ የሚሰራ መተግበሪያ እየሰራ መሆኑ ታውቋል።

ዋትስአፕ በአሁኑ ወቅትም በኮምፒውተር ላይ መስራት ይችላል የተባለውን መተግበሪያውን እየሞከረ መሆኑ ነው የተነገረው።

ከዚህ ቀደም ከስማርት ስልክ ጋር ተገናኝቶ ይሰራ የነበረው ዋትስአፕ አሁን መተግበሪያው ስራ ላይ እንዲውል ከተደረገ ያለ ስማርት ስልክ ዋትስአፕም መጠቀም ያስችላል ተብሏል።

ዋትስአፕ በአሁኑ ጊዜ በድረ ገጽ አማካኝነት መጠቀም የሚያስችል ቢሆንም፤ አገልግሎቱን ለማግኘት ግን ከስልካችን ጋር ማገናኘት የግድ ይለናል።

አሁን እየተሞከረ ያለው መተግበሪያ ግን ስልካችን ዝግ ቢሆንም እንኳ መጠቀም የሚያስችለን መሆኑ ነው የተነገረው።

ምንጭ፦ www.techworm.net

You might also like
Comments
Loading...