Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባን የሆቴል ኢንቨስትመንት መዳረሻና የኮንፈረንስ ማዕከል ለማድረግ የኮንቬንሽን ቢሮ ተቋቋመ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 13፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባን የሆቴል ኢንቨስትመንት ለማሳደግ እና ከተማዋን ግዙፍ የኮንፈረንስና የልዩልዩ ሁነቶች መስተናገጃ ወይም የማይስ ማዕከል ለማድረግ የኮንቬንሽን ቢሮ እንዲከፈት የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዛሬው ዕለት መደበኛ የካቢኔ ስብሰባውን አድርጓል፡፡

የኮንቬንሽን ቢሮ መከፈቱ የኮንፈረንስ ቱሪዝምን ለማሳደግ ፣ ኤግዚቢሽኖች ለማስፋት ፣ ለንግድ ትስስሮች እና ኩነቶች መጠናከር አስተዋፅኦ አንደሚያበርክት ተጠቁሟል፡፡

እንዲሁም ወደ ከተማዋ የሚመጡ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ደረጃውን በጠበቀ ፕሮቶኮል እንዲስተናገዱ ማስቻል የማይስ ማዕከል በመሆኗ የምታገኘው ጠቀሜታ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

በከተማው ካቢኔ የተቋቋመውን ይህን ማዕከል አቶ ቁምነገር ተከተል በዳይሬክተርነት እንዲመሩ የተሾሙ ሲሆን 50 ሺህ ብር የሚገመት ወርሃዊ የስራ ጊዜያቸውን ለከተማ አስተዳደሩ በነፃ ለማገልገልም ቃል መግባታቸውን አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

እንዲሁም ካቢኔው የ2012 ረቂቅ በጀት 47 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር እንዲሆን ወሰነ፡፡

ረቂቅ በጀቱ በአስተዳደሩ ምክር ቤት ቀርቦ ሲፀድቅ ወደ ስራ እንደሚገና ነው የተነገረው፡፡

እንዲሁም የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅትን በከፊል ወይም ሙሉለሙሉ ወደ ግል ለማዛወር ጥናት ተደርጎ እንዲቀርብም ውሳኔ አሳልፎዋል ::

You might also like
Comments
Loading...