Fana: At a Speed of Life!

አዕምሮን ከስልኮች ጋር የሚያገናኝ መሳሪያ ተዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 11፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢሎን ሙስክ የተባለው የቴክኖሎጂ ፈጣሪ በብሉትዝ የሚሰራ እና አዕምሮን ከስልክ ጋር የሚያገናኝ መሳሪያን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚፈልግ ይፋ አደረገ፡፡

ይህም ያለአካላዊ ግንኙነት የመረጃ ሽግግር ( ቴሌፓቲ) ተግባራዊ እንዲሆን እና ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ማገገም እንዲችሉ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ነው የተባለው፡፡

ይህ መሳሪያ እንደ ፀጉር ቀጭን አንደሆነ እና በሮቦት አማካኝነት በሰው አዕምሮ ላይ እንደሚቀመጥ ነው የተነገረው፡፡

አዘጋጁ መሳሪያውን ለማስቀመጥ ምንም አይነት ጭንቀት አይፈጥርም  ያሉ ሲሆን በጥሩ ሁኔታ እነደሚሰራ እና ገመድ አልባ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የሚቀመጡት አነስተኛ ቺፖች ያለምንም ገመድ መረጃውን ለጆሮ ማዳመጫ የሚያደርሱ ሲሆን ይህ የጆሮ ማዳመጫም መረጃውን ለስልክ መተግበሪያው ያደርሳል፡፡

በአሁን ወቅት የመሳሪያው ዋና አላማ የአዕምሮ በሽታዎች እና ሽባነትን ለመከላከል ያለመ ሲሆን በሂደት ግን ለአዕምሮ ቀዶ ጥገና  አማራጭ ይናል የሚል ተስፋ ተጥሎ በታል፡፡

አለማቸው ይህን በአዕምሮ ላይ የሚቀመጠው መሳሪያ ሂደት እንደ ጨረር የአይን ህክምና ቀላል እንዲሆን ለማስቻል መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

መሳሪያው ወይም ቺፑ ገመድ አልባ በመሆኑ በአዕምሮ ውስጥ ሊቀመጥ የሚችል ገመድ ባለመኖሩ ወሳኝ ነው ሲል ኢሎን ሙስክ ተናግረዋል፡፡

 

ምንጭ፡-ቢቢሲና ሲጂቲኤን

You might also like
Comments
Loading...