Fana: At a Speed of Life!

አካል ጉዳተኛ በመምሰል የማህበራዊ አገልግሎት ሰራተኞች አሰራርን የፈተሹት ከንቲባ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 17፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሜክሲኳዊው ከንቲባ ራሳቸውን አካል ጉደተኛ በማስመሰል እና እርዳታ እንደሚፈልጉ በማስመሰል የማህበራዊ አገልግሎት ሰራተኞችን አሰራር መፈተሻቸው ተሰምቷል።

ካውቴሞክ የተባለች ከተማ ከንቲባ የሆኑት ካርሎስ ቴና ይህንን ተግባር የፈፀሙት በተለይም አካል ጉደተኞች ከማህበራዊ አገልግሎት^ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ በርካታ ቅሬታዎችን በማቅረባቸው ነው ተብሏል።

ከንቲባ ካርሎስ ቴና በዊልቼር ወንበር ላይ በመሆን ወደ ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ በመሄድ ምግብ እንዲሰጡት የጠየቀ ሲሆን፥ ከተቋሙ ያገኘው ምላሽ ግን አስደንጋጭ እንደበበረ ነው የተነገረው።

አካል ጉዳተኛ መስሎ ወደ ስፍራው ያቀናው ከንቲባው በማህበራዊ አገልግሎት ሰራተኞቹ የጠየቀውን ምግብ ተከትክሎ ከስፍራው እንደተባረረ ነው የተነገረው።

ቅሬታውን ለማቅረብ ወደ ቢሮው አመራሮች ጋር ቢሄድም ፀሃፊዋ በንቀት ጠብቅ እንዳለችው እና ለ1 ሰዓት ከግማሽ ገደማ ማንም ሰው ወደ ስፍራው ብቅ እንዳላለም ተመልክቷል።

በመጨረሻም የደረሱትን ቅሬታዎች በአካል በመሄድ ካረጋገጠ በኋላ የለበሰውን በማወላለቅ ከዊልቼር ወንበሩ ለካይ በመነሳት የሄደ ሲሆን፥ ከንቲባው መሆኑን ባወቁበት ጊዜም ከፍተኛ ድንጋጤ እንደፈጠረባቸው ነው የተነገረው።

በራሱ ባደረገው ጥናት ችግሮችን የለየው ከንቲባው እስካሁን ለማንም ምንም እንዳልተናገሩ እና ምን አይነት እርምጃ ሊወስዱ እንደሚችሉ አለመገለጹ ነው የተነገረው።

ከንቲባ ካርሎስ ፔና በበኩሉ፥ ሁሉም ሰራተኞች ባይሆኑም የተወሰነሙት የተቋመኙ የስራ ባልደረቦቹ የሚሰሩት ስራ እንዳሳዘነው ተናግሯል።

ከዚህ በኋላ ከማንም ተገልጋይ ቅሬታን መስማት እንደማይፈልግ የተናገረው ከንቲባ ካርሎስ ፔና፥ ይህ ካልሆነ ግን ጥብቅ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ አስታውቋል።

ምንጭ፦ www.odditycentral.com

You might also like
Comments
Loading...