Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ስደተኞች ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ወደ መጡበት ሀገር መመለስ የሚያስችል መመሪያ አወጣች

አዲስ አበባ፣ሃምሌ 16፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ስደተኞች ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ወደ መጡበት ሀገር መመለስ የሚያስችል መመሪያ አወጣች።

የአሜሪካ መንግስት  ስደተኛች ፍርድ ቤት ቀርበው ውሳኔ ሳያገኙ ወደ መጡበት ሀገር  በፍጥነት ለመመለስ የሚያስችል መመሪያ አውጥታለች፡፡

መመሪያው ለሁለት ተከታታይ ዓመታት በሀገሪቱ  ውስጥ እንደነበር ማረጋገጥ ያልቻለን ስደተኛ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ሀገሩ እንዲመለስ የሚያደርግ ነው ተብሏል።

አሜሪካ እስካሁን ያለ ፍርድ ቤት ውሳኔ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የምታደርጋቸው ስደተኞች ከድንበሯ በቅርብ ርቀት ውስጥ በቁጥጥር ስር የዋሉና በሀገሪቱ  ከሁለት ሳምንት በታች የቆዩትን ብቻ ነበር።

ከዛሬው ዕለት ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል የተባለው ይህ መመሪያ፥ከተለያዩ ሀገራት ወደ አሜሪካ የሚያቀኑ ስደተኛችን ጫና ለመቀነስ ያስችላል ተብሏል።

በአንፃሩ አዲሱ መመሪያ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ስደተኞችን አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑ ተነግሯል።

ምንጭ ፦ቢቢሲ

You might also like
Comments
Loading...