Fana: At a Speed of Life!

ቻይና አሜሪካ ለታይዋን ለመሸጥ ያፀደቀችውን የጦር መሳሪያ ውል እንድትሰርዝ አስጠነቀቀች

አዲስ አበባ፣ሐምሌ 2፣ 2011(ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና አሜሪካ ለታይዋን ለመሸጥ ያፀደቀችውን የጦር መሳሪያ ውል ያለምንቅድመ ሁኔታ እንድትሰርዝ አስጠንቅቃለች።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሜሪካ ቻይና ሉአላዊ ግዛቴ ናት ለምትላት ታይዋን ለመሸጥ ያፀደቀችውን የ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር የጦር መሳሪያ ሽያጭ እንድትሰርዝ ጥሪ አቅርቧል።

የቻይና ዩውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጌንግ ሹአንግ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፥ አሜሪካ ለታይዋን ያፀደቀችውን የጦር መሳሪያ ሽያጭ የሀገሪቱን ሉዓላዊነት የሚዳፈር መሆኑን ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈም  ድርጊቱ በሀገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ላይ የሚደረግ አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነት ከመሆኑ በሻገር አለማቀፋዊ ህጉን የጣሰና የውጭ ግንኙነት ደንብ የተላለፈ መሆኑን ነው የገለጹት ።

ስለሆነም አሜሪካ ለታይዋን ለመሸጥ ያፀደቀቸውን የጦር መሳሪያ ሽያጭ ውል በፍጥነት ልትሰርዝ ይገባል ነው ያሉት ።

ቻይና አሜሪካ ለታይዋን ጦር መሳሪያ ለመሸጥ ስታቅድ ጀምሮ ድርጊቱ ተግባራዊ እንዳይሆን ስታስጠነቅቅ መቆየቷ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ አሜሪካ የቻይናን ማስጠንቀቂያ ወደ ጎን በመተው የጦር መሳሪያ ሽያጩን ማፅደቋ በበሀገራቱ መካከል ያለውን ግንኙነት ሊያሻክረው እንደሚችል በዘገባው ተመላክቷል።

ቻይና ራስ ገዝ የሆነውችውን ታይዋን የራሴ ግዛት ናት ብላ የምታምን ሲሆን፥ ይህን ለማሳካትም የተለያዩ ዘዴዎችን በመተግበር  ወደ ግዛቷ የማጠቃለል ፍላጎት አላት።

You might also like
Comments
Loading...