Fana: At a Speed of Life!

ትዊተር የጥላቻ ንግግርን የሚለቁ አካላትን ከገጹ እንደሚያግድ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የማህበራዊ ትስስር ድረ ገፅ የሆነው ትዊተር የጥላቻ ንግግር የሚነዙ ተጠቃሚዎችን ከገጹ እንደሚያግድ አስታወቀ።

በተለይም ከሀይማኖት ጋር በተያያዘ ሰብአዊነትን የሚያጎድፉ ይዘት ያላቸው መረጃዎችና እና ጽሁፎችን የሚለቁ አካላትን ሙሉ በሙሉ ከገጹ እንደሚያግድ ነው ያስታወቀው።

ኩባንያው ይህንን ለማድረግ የሚረዳው አዲስ ህግ ማውጣቱም ተነግሯል።

በአዲሱ የትዊተር ሀግ መሰረት ከዚህ በፊት በገጹ የተለቀቁ የጥላቻ ንግግሮችም ከገጹ እንዲነሱ እንደሚደረግ ታውቋል።

ሆኖም ግን ግለሰቦቹ የጥላቻ ንግግሮቹን የለቀቁት ህጉ ከመውጣቱ በፊት በመሆኑ ከገጹ እንደማይታገዱ ተነግሯል።

ትዊተር ከዚህ ቀደምም የመተግበሪያውን ህግና ደንብ የሚተላለፉ የሃገር መሪዎችና ፖለቲከኞች የሚያሰራጩትን መልዕክት ሊደብቅ መሆኑን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

ትዊተር ይህን ውሳኔ ያሳለፈው የተለያዩ ተፅዕኖ ፈጣሪ ፖለቲከኞች የመተግበሪያውን ህግና ደንብ በመጣስ ተገቢ ያልሆኑ መረጃዎችን ለተከታዮቻቻው በማሰራጨታቸው እንደሆነም ነው በወቅቱ የተጠቀመው።

ከዚህ በተጨማሪም ሀሰተኛ መረጃዎች እየተበራከቱ በመምጣታቸው ተከትሎ ችግሩን ከስሩ ለማድረቅ ትዊተር በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሀሰተኛ አካውንቶችን ማገዱም ይታወሳል።

ምንጭ፦ www.cnet.com

You might also like
Comments
Loading...