Fana: At a Speed of Life!

ቦሪስ ጆንሰን ቀጣዩ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆናቸው ተረጋገጠ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 16፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቦሪስ ጆንሰን ቀጣዩ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆናቸው በዛሬው እለት ተረጋግጧል።

ቦሪስ ጆንሰን የብሪታኒያ ገዢ ፓርቲ የሆነው የወግ አጥባቂ (ኮንሰርቫቲቭ ) ፓርቲ መሪ በመሆን የተመረጡ ሲሆን፥ በሀገሪቱ ህግ መሰረት የፓርቲው መሪ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሆን ይታወቃል።

የብሪኤግዚት አቀንቃኙ የቀድሞ የለንደን ከተማ ከንቲባ እና የብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ቦሪስ ጆንሰን የኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ መሪ ስፍራን ለመያዝ ከጀርሚ ሀንት ጋር ነበር የተፎካከሩት።

160 ሺህ የሚሆኑ የኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ አባላት የፓርቲውን መሪ ለመምረጥ በሰጡት ድምጽ ቦሪስ ጆንሰን 66 በመቶ ድምጽ በማግኘት ማሸነፋቸውም ታውቋል።

ይህንን ተከትሎም ቦሪስ ጆንሰን ነገ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር በመሆን እንደሚሾሙም ይጠበቃል።

ቦሪስ ጆንሰን ብሪታንያ ከአውሮፓ ሀብረት ጋር የፍቺ ስምምነት ላይ ባትደርስም በተቀመጠላት ቀን ትለያያለች የሚል አቋም አላቸው።

ይህንን አቋማቸውን የሚቃወሙ በርካታ የኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ አባላት የሆኑት የካቢኔ አባላትም ስራቸውን በራሳቸው ፍቃድ እንደሚለቁ መግለጻቸው ይታወሳል።

ምንጭ፦ www.aljazeera.com

You might also like
Comments
Loading...