Fana: At a Speed of Life!

በዶክተሮች ህይወቱ አልፏል የተባለው ወጣት ከሞት ተነሳ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  ህይወቱ እንዳለፈ የተነገረው የ20 ዓመት ወጣት ቀብሩ ሊፈፀም ሲል  ከሞት ወደ ህይወት መመለሱ ተነግሯል፡፡

የ20 ዓመቱ ወጣት ሙሀመድ ፉርቃን  ህይወቱ ማለፉ በህንድ የህክምና ባለሙያዎች  ተረጋግጦ እንደነበረ እና  የቀብር ስነ ስርዓቱ የተካሄደ በነበረበት ሰዓት  መነሳቱ በአካባበቢው ነበሩትን በእጅጉ አስደንግጧል፡፡

ከሞቱ ወደ ህይወት የተመለሰው ወጣት በቀጥታ ወደ ሆስፒታል እንደተላከ እና አየር እንዲያገኝ መደረጉ ነው የተነገረው፡፡

ፉርቃን  ባጋጠመው አደጋ ምክንያት በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከሰኔ 14 ጀምሮ እራሱን እንደማያውቅና ሰኞች ዕለት ዶክተሮች ህይወቱ እንዳለፈ ማረጋገጣቸው ተነግሯልል፡

ወደ ህይወት የተመለሰው ፉርቃን ሞት ድንጋጤ ፈጥሮባቸው የነበሩት ቤተሰቦቹ በቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ ወደ ህይወት መመለሱ ደግሞ ድንጋጤያቸውን ከፍ አድርጎታል፡፡

ቤተሰቦቹ ለወጣቱ ህክምና 10 ሺህ ዶላር ለሆስፒታል እንዲፍሉ  መጠየቃቸውን  የተናገሩ ሲሆን   ለዶክተሮች ገንዘብ እንደጨረሹ ሲገልፁላቸው  ፉርቃን ህይወቱ እንዳለፈ አረዱን ብለዋል፡፡

ይህ ሁኔታ ያጋጠማት በህንድ ሰሜናዊ ክፍል የምትገኘው ከተማ የህክምና አለቃ በጉዳዩ ዙሪያ ምርመራ እንደተጀመረ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፡- ፎክስ ኒውስ

You might also like
Comments
Loading...