Fana: At a Speed of Life!

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጎማ ከተማ ኢቦላ መከሰቱ ተረጋገጠ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 8፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በምስራቅ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጎማ ከተማ ኢቦላ መከሰቱ ተረጋገጠ፡፡

ቫይረሱ በአካባቢው ሊከሰት የቻለው አንድ ታማሚን ጨምሮ 18 ተሳፋሪዎችን ያሳፈረ ተሸክርካሪ በትናንትናው እለት ጠዋት ላይ ከቡተምቦ ተነስቶ ኖርድ ኪቩ ግዛት ውስጥ የመትገኘው ጎማ ከተማ መግባቱን ተከትሎ እንደሆነ ተነግሯል።

በዚህም ግለሰቡ ላይ በአፋጣኝ በተደረገ ምርመራ የኢቦላ ቫይረስ እንዳለበት የተረጋገጠ ሲሆን፥ ከታማሚው ጋር የተሳፈሩ መንገደኞች እና አሽከርካሪው ክትባት እንዲሰጣቸው መደረጉን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ጎማ ከተማ በሀገሪቱ በዓመቱ በሁለተኛ ደረጃ ቫይረሱ ስርጭት ከተመዘገበበት አካባበቢ በስተደቡብ አቅጣጫ የምትገኝ ሰፊ ከተማ መሆኗም ነው የተነገረው።

በጎማ ከተማ ቫይረሱ መከሰቱ በሩዋንዳ አወሳኝ አካባቢ እንደመሆኑ እና አካባቢው ህዝብ በሰፊው በሰፈረበት በመሆኑ በፍጥነት ይዘመታል ተብሎ ስጋት መፍጠሩም ተነግሯል።

በሀገሪቱ ምስራቅ አካባቢ1 ሺህ 655 ሰዎች በቫይረሱ ሲሞቱ 694 ያህሉ መፈዎሳቸውን እና 160 ሺህ 239 ዜጎች ክትባት እንዲወስዱ መደረጉን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር በቅርቡ ይፋ ያደረገው መረጃ ያመለክታል።

ይሁን እንጅ በአካበቢው ያለው የሰላም ሁኔታ የቫይረሱን መከላከል እና መቆጣጠር ስራ አስቸገሪ እንዳደረገው ነው ዘገባው የሚያመላክተው

ምንጭ፡- አልጀዚራ

You might also like
Comments
Loading...