Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ ዋንጫ ናይጄሪያ 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች

አዲስ አበባ፣ ሓምሌ11፣ 2011(ኤፍ ቢ ሲ) በግብፅ እየተካሄደ ባለው 32 ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ጨዋታ ናይጄሪያ 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።

ትናንት ምሽት በተደረገው የደረጃ ጨዋታ ናይጄሪያ ቱኒዚያን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ መርሃ ግብሩን አጠናቃለች።

የናይጄሪያን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብም ኦዲዮን ኢግሃሎ አስቆጥሯል።

ይህን ተከትሎም ኦዲዮን ኢግሃሎ በውድድሩ 5 ግቦችን በማስቆጠር በኮከብነት እየመራ ይገኛል።

በግብፅ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው 32 ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ነገ በሚደረገው የሴኔጋልና የአልጄሪያ የፍፃሜ ጨዋታ የሚጠናቀቅ ይሆናል።

ምንጭ፦ቢቢሲ

You might also like
Comments
Loading...