Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል በ2011/2012 የመኸር ዘመን ከ4 ሚሊየን ሄክታር በላይ ማሳ በዘር በመሸፈን ከ120 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 5፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአማራ ክልል በ2011/2012 የመኸር ወቅት 4 ነጥብ4 ሚሊየን ሄክታር ማሳ በዘር በመሸፈን ከ120 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ እየተሰራ ነው፡፡

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋሁን መንግስቱ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በአደረጉት ቆይታ በክልሉ በዘር ለመሸፈን ከታቀደው 4ነትብ 4 ሚሊየን ሄክታር መሳ መካከል 42 በመቶ ያህሉ በዘር መሸፈኑን ተናግረዋል፡፡

እቅዱን ለማሰካት በተዋረድ ከወረዳ አስከ ዞን ድረስ በቅንጅት እየተሰራ ነው ያሉት ሃላፊው በቆሉ ገብስና ድንች እና መሰል ሰብሎች መዘራታቸውን ገልጸዋል፡፡

በዘር ለመሸፈን ከታቀደው ማሳ መካከል 93 በመቶ ያህሉ ለመዘራት ዝግጁ ሆኗል ያሉት ኃፋው 2ነጥብ 8 ሚሊየን ሄክታር በመስመር፣ ለመዝራት ታቅዶ 993 ሺህ 994 ሄክታር መከናዎኑ እና ቀሪው 1ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር ማሳ በኩታገጠም ለማልማት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ለዚህም 5ነጥብ 3 ሚሊየን ኩንታል ማደበሪያ ለማቅረብ ታቅዶ እስካሁን 4ነጥብ 5 ሚሊየን ተሰራጭቷል ነው ያሉት፡፡

በምስራቅ ጎጅም ደቡብ እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞን የዩሪያና ዳፕ ማዳበሪያ እጥረት መከሰቱ የተገለጸ ሲሆን÷ ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ 500 ሺህ ኩንታል እንደሚጓገዋዝ ነው የተናገሩት ፡፡

እጥረቱ በተለይም ዩሪያ ላይ ሰፋ ያላ ሲሆን÷ ከ500 ሺህ ኩንታል ማዳበሪያው 400 ሺህ ያህሉ ዩሪያ በመሆኑ ችግሩን ይፈታል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡

በሙሃመድ አሊ

You might also like
Comments
Loading...