Fana: At a Speed of Life!

በህይወት ዘመናቸው አንድ ጊዜ በቆረጡት ሎተሪ የ3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር አሸናፊ የሆኑት ዕድለኛ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 10፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህይወት ዘመናቸው አንድ ጊዜ ብቻ ሎተሪ የቆረጡት ጡረተኛ የ3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ዕድለኛ መሆናቸውን የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር አስታውቋል።

በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ የሱፍ መሐመድ በልዩ ሎተሪ 1ኛ ዕጣ በሁለት ነጠላ ትኬቶች የ3 ሚሊየን 500 ሺህ ብር ዕድለኛ መሆን ችለዋል።

አቶ የሱፍ ሎተሪ ይደርሳል ብለው እንደማያስቡና “የውሸት ትርክት ነው” ብለው ያምኑ ስለነበር ሎተሪ ቆርጠው እንደማያውቁ ነው የተናገሩት።

ነገር ግን አንድ ቀን ሰፈራቸው አካባቢ ጫማ እያስጠረጉ የሎተሪ አዟሪ መጥቶ ሎተሪ ይግዙኝ ሲላቸው 20 ብር አውጥተው ነበር ልዩ ሎተሪን የቆረጡት።

ይህ በህይወት ዘመናቸው ለመጀመሪያ ጊዜ የቆረጡት ሎተሪ ግን እሳቸው ከሚያምኑት በተቃራኒ ሚሊየነር አድርጓቸዋል።

አቶ የሱፍ ጦረተኛ ሲሆኑ የሶስት ልጆች አባት ናቸው፡፡

በደረሳቸው ገንዘብም ምን እንደሚሰሩበት ሲናገሩ “ፈጣሪ የቤት ችግሬን አይቶ ይህን ገንዘብ ስለሰጠኝ ሳልውል ሳላድር ቤት ነው የምገዛበት” በማለት ተናግረዋል።

You might also like
Comments
Loading...