Fana: At a Speed of Life!

ሳምሰግ ታጣፊ ስልኩ ለሽያጭ ዝግጁ መሆኑን ገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 18 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳምሰንግ የመጀመሪያው ታጣፊ ስልክ  በመስከረም ወር ለሽያጭ እንደሚቀርብ ኩባንያው አስታወቀ፡፡

ታጣፊ የሳምሰንግ ስልክ ባለፈው ሚያዚያ ወር ላይ ለሽጭ ለማቅረብ ዝግጅት ተጠናቆ የነበረ ሲሆን የስክሪን ችግር በማጋጠሙ ወደ ገቢያ ሊቀርብበት የነበረው ጊዜ መራዘሙ የሚታወስ ነው፡፡

በተመረጡ ገቢያዎች በ2 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ለሽያጭ የሚቀርበው ታጣፊ ስልክ ማሻሻያዎች እንደተደረጉለት ነው ያስታወቀው፡፡

ሳምሰንግ ታጣፊ ስልኩን  ከተፎካካሪዎቹ ቀድሞ ለገቢያ ለማቅረብ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ እንደቆየ ነው የተነገረው፡፡

ኩባንያው በታጣፊው ስልክ ላይ የዲዛይን ግምገማ፣ አስፈላጊ ማሻሻያዎችን እና እና ተደጋጋሚ ፍተሻዎችን እንዳደረገም አስታውቋል፡፡

በታጣፊው ስልኩ  ላይ ተጨማሪ የመከላከያ ሽፋን የተደረገለት ሲሆን የስልኩ ማጠፊያ አካልን የማጠናከር ስራ እንደተከናወነ ተነግሯል፡፡

You might also like
Comments
Loading...