Fana: At a Speed of Life!

የወጣቶች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ንቅናቄ ነገ በአሶሳ ከተማ ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮው የወጣቶች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ንቅናቄ ነገ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ እንደሚጀመር የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ አስታወቀ፡፡

የሊጉ ምክትል ፕሬዚዳንትና የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አባንግ ኩመዳን በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት÷በዘንድሮው የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት 8 ሚሊየን በላይ ወጣቶች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በዘንድሮው የክረምት ወቅት ወጣቱ በተለያዩ አገልግሎቶች በመሳተፍ አሻራውን እንዲያሳርፍ ዝግጅች ተደርጓል ያሉት ሃላፊዋ÷ለዚህም ነገ የንቅናቄው ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በአሶሳ ይካሄዳል ነው ያሉት።

ወጣቶች በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር፣ በአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት፣ በጤና ተቋማት ሕህሙማን ድጋፍ፣ በደም ልገሳ መርሐ ግብር እና በሌሎች ተግባራት እንደሚሳተፉ ጠቁመዋል፡፡

በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ400 ሚሊየን በላይ ችግኝ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመትከል መታቀዱንም አመላክተዋል፡፡

በሳሙኤል ወርቃየሁ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.