Fana: At a Speed of Life!

የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሱዳን ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሱዳን ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ መሆናቸው ተነገረ።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጉብኝቱን የሚያደርጉት በሱዳን የሽግግር መንግስት ሉአላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሌተናል ጄኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን በቀረበላቸው ግብዣ ነው።

በፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የተመራው የኤርትራ መንግስት ልኡካን ካርቱም ሲገቡም ሉአላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሌተናል ጄኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በካርቱም ቆይታቸውም የሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት የሚያደርጉ መሆኑን የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገፃቸው አስታውቀዋል።

ፕሬዚዳንቱ በሱዳን ቆይታቸውም የኤርትራን እና የሱዳንን የሁለትዮሽ ትብብሮችን ማጠናከር በሚቻልባቸው ላይ የሚመክሩ ሲሆን፥ በቀጠናዊ ትብብር እና ውህደት ዙሪያ ውይይቶችን እንደሚያደርጉም አስታውቀዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.