Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አበይ አህመድ ለተሰው ከፍተኛ የሲቪልና የመከላከያ አመራሮች የማስታወሻ ችግኝ ተከሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አበይ አህመድ ባሳለፍነው ሳምንት ለተሰው ከፍተኛ የሲቪልና የመከላከያ አመራሮች ማስታወሻ ችግኝ ተከሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አበይ ባሳለፍነው ሳምንት በባህር ዳር እና በአዲስ አበባ የተሰው አመራሮችን ማስታወሻ ነው በዛሬው እለት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የወይራ ዛፍ ችግኝ የተከሉት።

የወይራ ዛፍ ችግኞቹንም በዶክተር አምባቸው መኮንን፣ በጄነራል ሰዓረ መኮንን፣ በአቶ ምግባሩ ከበደ፣ በአቶ እዘዝ ዋሴ እና በሜጀር ጄነራል ገዛኢ አበራ ስም መተከላቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በዛሬው እለት የተካሄደው የችግኝ ተከላም የተሰው ከፍተኛ የሲቪልና የመከላከያ አመራሮች ለማስታወስ እና በሀገሪቱ በተካሄደው ለውጥ ውስጥ ለነበራቸው አስተዋጽኦ ቋሚ ማስታወሻን ለማኖር መሆኑንም ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።

You might also like
Comments
Loading...