Fana: At a Speed of Life!

የጤና ሚኒስቴር ከዛሬ ጀምሮ ጤና ተቋማት ከሲጋራ ጭስ ነጻ መሆናቸውን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ከዛሬ ጀምሮ ጤና ሚኒስቴር፣ ኤጀንሲዎች እና ፌደራል ሆስፒታሎች ከሲጋራ ጭስ ነጻ መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በሚኒስቴሩ፣ በጤና ኤጀንሲዎች እና ሆስፒታሎች ከዛሬ ጀምሮ ሲጋራ ማጨስ መከልከሉን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ይህን የሚገልጽ ማስታወቂያም በሚኒስቴሩ ግቢ በግልጽ አስቀምጧል።

አዲሱ የምግብ እና የመድኅኒት አስተዳደር አዋጅ አንቀጽ 48/1 የተቀመጠውን ድንጋጌ መነሻ በማድረግ ከበር መልስ ባሉ የህዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች ማጨስን ይከለክላል።

ከዚህ ባለፈም በህዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች ትንባሆ የማጨስ ክልከላን በተመለከተ ግልጽ እና ጎላ ያሉ ማስታወቂያዎች እንዲቀመጡ መደንገጉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like
Comments
Loading...