Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሶማሊያ ጋሮዌ ከተማ በረራ ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሶማሊያ ጋሮዌ ከተማ በረራ ሊጀምር ነው፡፡
 
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሞቃዲሾ ከሚያደርገው በረራ በተጨማሪ ወደ ጋሮዌ በረራ በመጀመሩ ታላቅ ደስታ እንደተሰማቸው ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ተወልደ ገብረማሪያም ገልጸዋል፡፡
 
ወደ ጋሮዌ በረራ መጀመሩ በሁለት ሀገራት መካከል ያለውን ኢኮሚያዊ፣ ፓለቲካዊ እና ማህበራዊ ግንኙነት የበለጠ ያጠናክራል ብለዋል ዋና ስራ አስፈፃሚው፡፡
 
እንዲሁም በአውሮፓ፣ አሜሪካ፣ ኢሲያ እና በሌሎች የአለም ሀገራት የሚገኙ የሶማሊያ ዲያስፖራዎች በቀላሉ በአዲስ አበባ በኩል ወደ ትውልድ ስፍራቸው እንዲበሩ ያስችላል ብለዋል፡፡
 
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁን ወቅት ከ120 በላይ ወደ ሚሆኑ የአለም አቀፍ መዳረሻዎች በረራ እያደረገ ይገኛል፡፡
 
በረራው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የአየር ትራንስፖርት መጠን ከፍ ለማድረግ እና ሶማሊያ በትራስፖርት ዘርፉ በበአለም አቀፍ ደረጃ ተዳጋጋሚነት እንዲኖራትም ያስችላል ነው የተባለው፡፡
You might also like
Comments
Loading...