Fana: At a Speed of Life!

ከቻይናዋ ቾንግቺንግ ወደ አዲስ አበባ የመጀመሪያው የጭነት በረራ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከቻይናዋ ቾንግቺንግ ወደ አዲስ አበባ የመጀመሪያው የጭነት በረራ መደረጉ ተገለፀ።

የመጀመሪያው የጭነት በረራ ከቻይና ቾንግቺንግ በህንድ ዋና ከተማ ደልሂ በኩል ወደ አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ትናንት መደረጉ ተገልጿል፡፡

በትናንትናው እለት የተደረገው የመጀመሪያው በረራ 103 ቶን በቾንግቺንግ የተመረቱ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችና እና ጨርቃ ጨርቆችን ጭኖ ነበርም ተብሏል።

በረራው የሚመራው በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲሆን፥ በየሳምንቱ ሁለት ጊዜ በረራ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

የበረራው መጠን እንደአስፈላጊነቱ ማስተካከያ እንደሚደረግበትም ተጠቁሟል።

አዲሱ በረራ በቾንግኪንግ እና በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ልውውጥን የበለጠ ያጠናክረዋል ተብሎ እንደሚጠበቅም የቾንግቺንግ ጂንግበይ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን አስታውቋል”

ምንጭ፦ www.xinhuanet.com

You might also like
Comments
Loading...