Fana: At a Speed of Life!

ትዊተር የመተግበሪያውን ደንብ የሚጥሱ ፖለቲከኞችን መልዕክት ሊደብቅ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ትዊተር የመተግበሪያውን ህግና ደንብ የሚተላለፉ የሃገር መሪዎችና ፖለቲከኞች የሚያሰራጩትን መልዕክት ሊደብቅ መሆኑን ይፋ አድርጓል።

ትዊተር ይህን ውሳኔ ያሳለፈው የተለያዩ ተፅዕኖ ፈጣሪ ፖለቲከኞች የመተግበሪያውን ህግና ደንብ በመጣስ ተገቢ ያልሆኑ መረጃዎችን ለተከታዮቻቻው በማሰራጨታቸው ነው ተብሏል።

ባለስልጣናቱና የሃገር መሪዎች የሚያስተላልፉት አሳሳችና የሚያምታታ መልዕክት ዜጎችን ለተለያዩ ጉዳቶች መዳረጉን በአስረጅነት ጠቅሷል።

ስለሆነም መሰል ድርጊቶችን ለማስወገድ ትዊተር ተፅዕኖ ፈጣሪ ባለስልጣናት ህግና ደንቡን በመጣስ የሚያስተላልፏቸው መረጃዎች ለተከታዮቻቸው እንዳይደርሱ የሚያደርግ መሆኑን አስታውቋል።

ይህ ሲደረግም ለደንበኞቹ ምንም አይነት የማሳወቂያ መልዕክት የማይደርሳቸው መሆኑም ነው የተገለፀው።

ውሳኔውም ከትናንትናው ዕለት ጀምሮ በሚሰራጩ መረጃዎች ላይ ብቻ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑ ተገልጿል።

 

ምንጭ ፦ቢቢሲ

You might also like
Comments
Loading...