Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ከአውሮፓ ህብረት የሰብዓዊ መብት ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 5 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከአውሮፓ ህብረት የሰብዓዊ መብት ልዩ መልዕክተኛ ኤሞን ጊልሞር ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸው ወቅትም ኢትዮጵያና የአውሮፓ ህብረት በመሰረቱት ስትራቴጂካዊ አጋርነት ላይ ትኩረት አድርገው መክረዋል።

ህብረቱ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ለሚገኙ የማሻሻያ ስራዎች አድናቆት እንዳለው ልዩ መልዕክተኛው በዚህ ወቅት ገልጸዋል።

በቀጣይም ህብረቱ ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 

You might also like
Comments
Loading...