Fana: At a Speed of Life!

ጀርመንና ኔዘርላንድስ በኢራቅ የሚሰጡትን ወታደራዊ ስልጠና አቋረጡ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጀርመንና ኔዘርላንድስ በኢራቅ ሲሰጡት የነበረውን ወታደራዊ ስልጠና ማቋረጣቸው ተሰምቷል።

ጀርመን በኢራቅ  ስትሰጠው የነበረውን ወታደራዊ ስልጣና ማቋረጧን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጄንስ ፍሎስዶርፍ ተናግረዋል።

ሀገሪቱ ስልጠናውን ያቋረጠችውም በቀጠናው በአሜሪካና ኢራን መካከል ያለው ፍጥጫ እያየለ በመምጣቱ በአካባቢው ያለው የሰላምና ደህንነት ሁኔታ ስጋት ላይ መውደቁ ነው ተብሏል።

ይሁን እንጂ ጀርመን ያቋረጠችው ወታደራዊ ስልጠና በቅርቡ የምትቀጥል መሆኑን ቃል አቀባዩ ጠቁመዋል።

ኔዘርላንድስ በበኩሏ በአካባቢው በተደቀነው የደህንነት ችግር ምክንያት ወታደሮቿ በኢራቅ የሚሰጡትን ወታደራዊ ስልጠና እንዲያቆሙ ማድረጓን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ስልጠና ሲሰጡ የነበሩት ወታደሮቿም ቆይታቸውን ቤት ውስጥ እንዲያደርጉ ትዕዛዝ ማስተላለፏ ተገልጿል።

ጀርመን በኢራቅ 160 የሚሆኑ ወታደሮች ያሰማራች ሲሆን፥ኔዘርላንደስ ደግሞ 170 የሚሆኑ ወታደሮችና ሲቭል ሰራተኞችን አሰማርታለች ።

በቅርቡ አሜሪካ የተለያዩ ጦር መሳሪያ የጫኑ መርከቦችንና ወታደሮችን ወደ መካከለኛው ምስራቅ መላኳን ተከትሎ ከኢራን ጋር ያላት እሰጣገባ እየጨመረ መጥቷል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል በተፈጠረው ውጥረት ምክንያትም በቀጠናው ያለው የሰላምና ደህንነት  ስጋት አሳሳቢ መሆኑ እየተነገረ ነው።

ምንጭ ፦PressTv.com

 

You might also like
Comments
Loading...