Fana: At a Speed of Life!

የጤና  ሚኒስቴር እና ጀኔራል ኤሌክትሮኒክስ የህክምና መሳሪያዎች አምራች ድርጅት በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2011 (ኤፍ ቢሲ) የጤና ሚኒስቴር እና ጀኔራል ኤሌክትሮኒክስ የህክምና መሳሪያዎች አምራች ድርጅት በጤናው ዘርፍ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ተስማሙ።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን ከጀኔራል ኤሌክትሮኒክስ የህክምና መሳሪያዎች አምራች ድርጅት ሃላፊዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

በዚህም ከጀኔራል ኤሌክትሮኒክስ የህክምና መሳሪያዎች አምራች ድርጅት ጋር በሀገር አቀፍ ደረጃ በ3 ዓመታት ጊዜ ውስጥ 100 የሜዲካል ኦክስጅን ማምረቻና ማከፋፈያዎችን በመንግስትና በግል አጋርነት ለመገንባት ስምምነት ላይ መደረሱ ተገልጿል።

ከዚህ ባለፈም በሀገሪቱ የሚገኙ የህክምና መሳሪዎችን የመከላከል እና የብልሽት ጥገና አገልግሎት ለመስጠት ስምምነት ላይ ተደርሷል ነው ያሉት ዶክተር አሚር ።

በተጨማሪም በኢትዮጵያ የህክምና መሳሪያዎች መገጣጠሚያ ፋብሪካ ለመክፈት በሚያስችሉ መንገዶች ላይ ውይይት መደረጉን ዶክተር አሚር አስታውቀዋል።

 

You might also like
Comments
Loading...