Fana: At a Speed of Life!

የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት ወራት 163 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን ገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 15፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት ወራት 163 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ የግብር ህግ ተገዢነትን ለማረጋገጥ ከዘርፍ ተዋናዮች ጋር በአዲስ አበባ ውይይት እያካሄደ ነው።

በውይይቱም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከዘርፍ ተዋናዮች ጋር በታክስ አስተዳደር ችግሮችና መደረግ ባለባቸው መፍትሄዎች ዙሪያ ምክክር እየተካሄደ ነው።

በዚህም ወቅትም የታክስ አሰባሰብ ስርዓቱን በንቅናቄ በመምራት ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ9 ነጥብ 8 በመቶ እድገት ያሳየ አፈፃፀም መመዝገቡ ተገልጿል።

ሚኒስቴሩ ባለፍት ጊዜያት በሀሰተኛ ደረሰኝ ሲሰሩ የነበሩ 124 ድርጅቶች ላይ ህግ የማስከበር ስራ መስራቱ የተገለፀ ሲሆን፥ ድርጅቶቹ 6 ቢሊየን ብር የመንግስት ሀብት ላይ ጉዳት አድርሰዋል ተብሏል።

በተመሳሳይ ማጭበርበር ውስጥ የተገኙ 68 ድርጅቶችም ጉዳያቸው እየተጣራ ነው ተብሏል።

ከለውጡ በኋላ የታክስ አስተዳደር ለማሻሻል እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት በዝርዝር እየቀረበ ሲሆን፥ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት የሚደረግበት መሆኑም ተገልጿል።

ኃይለየሱስ መኮንን

You might also like
Comments
Loading...