Fana: At a Speed of Life!

የውኃ አካላት መጨመር 100 ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎች እንዲፈናቀሉ ሊያደርግ ይችላል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2011(ኤፍ.ቢ.ሲ) የውኃ አካላት ከሚጠበቀው በላይ መጨመር የዓለም ስጋት መሆኑ ተገለጸ፡፡

የግሪን ላንድና አንታርክቲክ የበረዶ ግግር መቅለጥ ውቅያኖሶች መጠን እየጨመረ እንደሚገኝና ለአለማችን ስጋት እንደደሆነ ተመራማሪዎች አስጠንቅቀዋል፡፡

ይህም በአውሮፓዊያኑ 2100 የውቅያኖሶችን ከፍታ በአንድ ሜትር ያህል ከፍ ሊያደርገው እንደሚችል ነው ተመራማሪዎች ስጋታቸውን የሚያስቀምጡት፡፡

ከዚህ ችግር ጋር በተያያዘ በመቶ ሚሊየን የሚገመቱ ዜጎችን ሊፈናቀሉ እንደሚችልም አስገንዝበዋል፡፡

ለችግሩ መባባስ የአካባቢ ብክለት ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዝ ሲሆን÷ በሚቀጥሉት 80 አመታት የዓለም የውኃ አካላት መጠን ከ52 ሴንቲ ሜትር እስከ 98 ሴንቲ ሜትር ሊጨምር እንደሚችልም ተገምቷል፡፡

የከባቢ ብክለቱ በዚሁ ከቀጠለ የውቅያኖሶችን መጠን እስከ አውሮፓውያኑ 2100 ከ62 እስከ 238 ሴንት ሜትር ሊጨምር ይችላል ተብሏል፡፡

1 ነጥብ 79 ሚሊየን ስኩዌር ኪሎ ሜትር የመሬት አካልም በውሃ ሊሸፈን ይችላል የሚል ስጋት አለ፡፡

ምንጭ፡- ቢ ቢ ሲ

 

You might also like
Comments
Loading...