Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ አውሮፓ የቢዝነስ ፎረም በብራሰልስ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮ አውሮፓ የቢዝነስ ፎረም በብራሰልስ መካሄድ ጀመረ፡፡

ይህ የቢዝነስ ፎረም በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት አማራጭ ለመጠቀም ፍላጎት ያሳዩ አውሮፓውያን ኢንቨስተሮች በአንድ ለማግኘት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

በፎረሙ ታዋቂው የመኪና አምራች ቮልስዋገን እና ምግብ፣ መጠጥ፣ የውበት መጠበቂያ እና ሌሎችን ምርቶችን በማምረት የሚታወቀው የዩኒሌቨር ኩባንያ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በዚህም በኢትዮጵያ ባለው ከፍተኛ ገቢያ፣ የኢንቨስትነት መዳረሻዎች እና በኢትዮጵያ ያለውን የጥሬ እቃዎችን በተመለከተ ውይይት ተደርጓል፡፡

በብራሰልስ እየተካሄደ በሚገኘው የቢዝነስ ፎረም የኢትዮጵያውያን ኢንቨስተሮች እየተሳተፉ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አበበ አበባየሁ አስታውቀዋል፡፡

በዛሬው ዕለት መካሄድ የጀመረው ይህ የቢዝነስ ፎረም እስከ ነገ ድረስ የሚካሄድ መሆኑን ከወጣው መርሃ ግብር ለማወቅ ተችሏል፡፡

You might also like
Comments
Loading...