Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ልዑካን ስዊዘርላንድ በተዘጋጀው 72ተኛው የጤና ዓለም አቀፍ ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ነው

አዲስ አበባ ግንቦት 12፣ 2011(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በጄኔቫ ስዊዘርላንድ እየተካሄደ በሚገኘው 72ኛው የጤና ዓለም አቀፍ ጉባዔ በመሳተፍ ላይ ይገኛል።

በበጄኔቫ በሚካሄደው 72ኛው የጤና ዓለም አቀፍ ጉባዔ ለመሳተፍ በጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን የተመራ ልዑክ ወደ ጄኔቫ አቅንቷል።

ኢትዮጵያ በጉባዔው ላይ ሁለት አዳዲስ ለውሳኔ የሚቀርቡ ሀሳቦችን ማዘጋጀቷን ዶክተር አሚር አማን አንስተዋል።

እንዲሁም ከጉባዔው ጎን ለጎን የሚካሄዱ ሁለት ስብሰባዎችን በማዘጋጀትም ትመራለች።

የመጀመሪያ ጤና ክብካቤ ለሁለንተናዊ የጤና ሽፋን እና ለዘላቂ የልማት ግቦች መሳካት በሚል ርዕስ ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሀገራት ጋር በጋራ በመሆን ያዘጋጀችው የውይይት መድረክ  አንዱ ነው።

የልዑካኑ ቡድኑ ከሌሎች ሀገራት ጋር የልምድ ልውውጥ እና አዳዲስ ትብብሮችን ለመፍጠር ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር ውይይት እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

ዶክተር አሚር ኢትዮጵያ የምትከተለው ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን /ወረዳ ትራንስፎርሜሽን እቅድ/ የብዙ ዘርፎች እና የባለድርሻ አካላትን ትብብር የሚጠይቅ መሆኑንም ገልጸዋል።

You might also like
Comments
Loading...