Fana: At a Speed of Life!

ወልዋሎ ከወላይታ ዲቻ እንዲሁም መከላከያ ከጊዮርጊስ አቻ ተለያይተዋል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬ ሁለት ጨዋታዎችን አስተናግዷል።

ወልዋሎ አዲግራት በሜዳው ወላይታ ዲቻን አስተናግዶ ጨዋታውን ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት አጠናቋል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም ደግሞ 10 ሰዓት ላይ መከላከያ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫውተዋል።

በጨዋታው ቅዱስ ጊዮርጊስ 1 ለ 0 ሲመራ ቢቆይም መከላከያ በ2ኛ አጋማሽ ባስቆጠረው ጎል ጨዋታውን በአቻ ውጤት ጨርሷል።

ነገ በተለያዩ ከተሞች 5 ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

ትናንት በተካሄደ አንድ ጨዋታ በፕሪሚየር ሊጉ ግርጌ የሚገኘው ደደቢት ባህር ዳር ከተማን ማሸነፉ ይታወሳል።

ሊጉን መቐለ 70 እንደርታ በ48 ነጥብ ሲመራው ፋሲል ከነማ በ46 እንዲሁም ሲዳማ ቡና በ43 ነጥብ ይከተላሉ።

ደደቢት፣ ስሑል ሽረ እና ደቡብ ፖሊስ ደግሞ በደረጃው ግርጌ ተቀምጠዋል።

You might also like
Comments
Loading...