Fana: At a Speed of Life!

ከእንግሊዝ ተነስተው ወደ ጣልያን ሲያሽከረክሩ የነበሩት አዛውንት እራሳቸውን ጀርመን አገኙት

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከእንግሊዝ ኒውካስትል በመነሳት ወደ ጣሊያኗ ሮም እያሽከረከሩ የነበሩት አዛውንት ራሳቸውን አነስተኛ የጀርመን መንደር ውስጥ ማግኘታቸው ተነግሯል፡፡
በሳተላይት መመሪያ ችግር ምክንያት እራሳቸውን ጀርመን ያገኙት የ81 ዓመቱ አዛውንት ሉወይጂ ሪሞንቲ ይባላሉ፡፡
የተለያዩ ሚዲያዎችም አጋጣሚውን በመንተራስ መንገዶቹ ሁሉ ወደ ሮም ያመራሉ የሚለውን ጥንታዊ አባባል በማስታወስ እየዘገቡት ይገኛሉ፡፡
የ81 ዓመቱ አዛውንት ከሰሜን እንግሊዝ ተነስተው በአቋራጭ ወደ ሮም እየተጓዙ እንደነበረ ነው የተነገረው፡፡
ነገር ግን የሮማውን ሊቀጳጳስ ለማግኘት ወደ ሮም ሲያሽከረክሩ የነበሩት አዛውንት እራሳቸውን አነስተኛ በምትባልና ከኮሎኝ ምስራቅ የሰዓታት ጉዞ በኋላ በምትገኛ ከተማ ራሳቸውን ሊያገኙ ችለዋል፡፡
በወቅቱ በተመለከቱት ነገር ግራ የተጋቡት አዛውንቱ የእጅ ፍሬን መያዛቸውን በመዘንጋት ጉዳት ደርሶባቸዋል።
አዛውንቱ መኪናቸው ላይ የደረሰውን ጉዳት ጥገና ከተደረገለት በኋላ ወደ ጀመሩት የሮም ጉዞ ይቀጥላሉ ተብሏል፡፡
ምኝጭ፡-ስካይኒውስ

 

You might also like
Comments
Loading...