Fana: At a Speed of Life!

ኦማር ሃሰን አልበሽር ክስ ተመሰረተባቸው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 5 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ተሰናባቹ የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሃሰን አልበሽር ክስ ተመሰረተባቸው።

ክሱ የእርሳቸውን አስተዳደር በመቃወም አደባባይ በመውጣት ህይዎታቸው ካለፈ የሃገሬው ዜጎች ጋር የተያያዘ መሆኑ ተነግሯል።

አልበሽር በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ ጣልቃ በመግባት ለዜጎች ህልፈት ምክንያት ናቸው በሚል መከሰሳቸውን አቃቤ ህግ አስታውቋል።

ስለ ክሱ ዝርዝር ጉዳይ ግን እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

ኦማር ሃሰን አልበሽር ሱዳንን ለ30 አመታት ያክል መርተዋታል።

ባለፈው ሚያዚያ ወር መጀመሪያ ላይም በህዝባዊ ተቃውሞ ከስልጣን ወርደዋል።

አሁን ላይ በማረሚያ ቤት የሚገኙት አልበሽር ከህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርና ሽብርተኝነትን ይደግፋሉ በሚል ተጠርጥረው ጉዳያቸው እየተጣራም ይገኛል።

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like
Comments
Loading...