Fana: At a Speed of Life!

ኢንጂነር ታከለ ኡማ የማምረቻ ሼድ ተሰጥቷቸው በስራ ላይ የሚገኙ የወጣት ማህበራትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ምከተል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የማምረቻ ሼድ ተሰጥቷቸው በስራ ላይ የሚገኙ የወጣት ማህበራትን ጎበኙ።

ምከተል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የማምረቻ ሼድ ውስጥ በተለያየ የስራ ዘርፍ የተሰማሩ የወጣት ማህበራትን ነው በዛሬው እለት የጎበኙት።

በጉብኝታቸውም በጫማ ማምረት፣ በወረቀት ስራ፣ በሽመና ስራ እና በልብስ ስፌት ስራ ላይ የተሰማሩ ለበርካታ የአከባቢው ወጣቶች የስራ ዕድል የፈጠሩ ማህበራትን ተዘዋውረው መመልከታቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በጉብኝቱ ላይ የየስራ ማህበራቱ ተወካዮች የማምረቻ ማዕከል ጥበት እና የገበያ ትስስር ችግር እንዳለባቸው ምከተል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገልፀዋል።

ኢንጂነር ታከለ ኡማ በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ ለስራ ማህበራቱ የገበያ ትስስርን ለመፍጠር እንደሚሰራ እና ልዩ ድጋፍ እንደሚያደርግም ተናግረዋል።

You might also like
Comments
Loading...