Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ዜጎቿ ወደ ኢራቅ እንዳይጓዙ አስጠነቀቀች

አዲስ አበባ፣ግንቦት 5፣2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በባግዳድ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የሀገሪቱ ዜጎች ወደ ኢራቅ ከሚደረግ ጉዞ እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

ኤምባሲው ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ  በመካከለኛው ምስራቅ  በተፈጠረው ውጥረት  ምክንያት የአሜሪካ ዜጎች ወደ ኢራቅ ምንም አይነት ጉዞ እንዳያደርጉ አስታውቋል።

በኢራቅ የሚገኙ የሀገሪቱ ዜጎችም አሜሪካውያን በብዛት ይሰበሰቡባቸዋል ተብለው ከሚታወቁ ቦታዎች ከመሄድ እንዲቆጠቡ  አስጠንቅቋል።

ሰሞኑን አሜሪካ ኢራቅ በቀጠናው ለምታደርገው ትንኮሳ አፀፋዊ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል የተለያዩ የጦር መሳሪያ የጫኑ መርከቦችን ወደ መካከለኛው ምስራቅ መላኳ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ በሁለቱ ሀገራት መካከል ከፍተኛ ውጥረት መንገሱ እየተነገረ ።

ባግዳድ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲም ከላይ በተጠቀሰው ችግር ምክንያት በመካከለኛው ምስራቅ ከፍተኛ የደህንነት ስጋት መኖሩን በመግለጫው አመላክቷል።

ስለሆነም የአሜሪካ ዜጎች ወደ ኢራቅ ከሚደረግ ማንኛውም ጉዞ እራሳቸውን እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

ምንጭ ፦አናዶሉ

You might also like
Comments
Loading...