Fana: At a Speed of Life!

ቻይና የተከለከለ አማቂ ጋዝ ወደ ከባቢ አየር በመልቀቅ ውንጀላ ቀረበባት

አዲስ አበባ ግንቦት 16፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቻይና “ትራይክሎሮፍሎሮ ሚቴን” የተባለውን የተከለከለ አማቂ ጋዝ በብዛት ወደ ከባቢ አየር በመልቀቅ ውንጀላ ቀርቦባታል፡፡

ጋዙ በተፈጥሮ የማይገኝና ለማቀዝቀዣና ለአየር ሙቀት ማስተካከያ ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን፥ ከባቢ አየርን በማሳሳትና ሙቀትን በማመቅ የከፋ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ይነገራል፡፡

በካናዳ ሞንትሪያል በተደረሰው ስምምነት መሰረትም ጋዙ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዳይመረትና ወደ ከባቢ አየር እንዳይለቀቅ እገዳ ተጥሎበታል።

ይሁን እንጅ ቤጂንግ ጋዙን ከ2013 ጀምሮ በብዛት ወደ ከባቢ አየር መልቀቋን በጉዳዩ ላይ የተደረገ አንድ ጥናት አመላክቷል።

ጋዙ ከሰሜን ምስራቅ ቻይና አሁንም ወደ ከባቢ አየር እየተለቀቀ መሆኑንም ነው ጥናቱ ያመላከተው።

ጥናቱ ከደቡብ ኮሪያና ጃፓን ከከባቢ አየር ላይ በተወሰዱ ናሙናዎች ላይ የተሰራ ነው ተብሏል፡፡

ባሳለፍነው የአውሮፓውያኑ ግንቦት ወርም ተመራመሪዎች ከሃዋይ ደሴት አካባቢ በወሰዱት የአየር ናሙና ከምስራቅ እስያ አካባቢ “የትራይክሎሮፍሎሮ ሚቴን” ልቀት እንዳለ ማረጋገጣቸውን ዘገባው አስታውሷል።

ምንጭ፡- አልጀዚራ

You might also like
Comments
Loading...