Fana: At a Speed of Life!

ትራምፕ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ብሄራዊ የአደጋ ጊዜ አዋጅ አወጁ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ኮምፒውተር ኔትወርክን ከውጭ ኃይሎች ጥቃት ለመከላከል ብሄራዊ የአደጋ ጊዜ አዋጅ አወጁ።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ኩባንያዎች የውጭ ሀገራት የቴሌኮም ቴክኖሎጂ ውጤቶችን እንዳይጠቀሙ የሚያደርገውን ይህን አዋጅ በፊርማቸው አፅድቀዋል።

ይህ አዋጅ በሀገሪቱ ላይ ሊከሰት የሚችልን ብሄራዊ የደህንነት አደጋ ለማቆም ያስችላል የሚችል እምነት ተጥሎበታል።

ሆኖም አዋጁን ተከትሎ የትኛዎቹ የኩባንያ ምርቶች ጥቅም ላይ እንዳይወሉ እንደተወሰነ ባይታወቅም የሁዋዌ ምርቶችን ኢላማ ያደረጋ ሳይሆን አይቀርም የሚል ግምት አለ።

ሁዋዌ በአሜሪካ የተጣለበት ገደብ አሜሪካውያን ደንበኞቹን እና ኩባንያዎችን ብቻ ሊጎዳ የሚችል ነው ሲል ውሳኔውን አጣጥሏል።

አሜሪካ እና አጋሮቿ ሁዋዌ የሚያመርታቸው ምርቶች ቻይና ለስለላ እየተጠቀመችባቸው ትገኛለች በማለት ቅሬታቸውን ሲገልፁ መቆየታቸው የሚታወስ ነው።

ምንጭ፡- ቢቢሲ

You might also like
Comments
Loading...