Fana: At a Speed of Life!

ቱርክ ኩባንያዎቿ በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ አበረታታለሁ አለች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቱርክ ኩባንያዎቿ በኢትዮጵያ እያደገ በሚገኘው የምግብ ማቀነባበሪያ ዘርፍ እንዲሰማሩ እንደምታበረታታ በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ያፕራክ አልፋ ተናገሩ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ከ18 ሀገራት የመጡ 151 አምራቾች የሚሳተፉበት አውደ ርዕይ እየተካሄደ ይገኛለ።

በዚህ ወቅት አምሳደሯ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በግብርናው ዘርፍ ለሚሰማሩ ኩባንያዎች ጥሩ የገበያ እድል እየፈጠረ እንደሚገኝ እና አዳጊ ኢኮኖሚ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ቱርክ ኩባንያዎቿ በኢትዮጵያ እንዲሰማሩ ድጋፍ ማድረጓን እንደምትቀጥል የገለፁት አምባሳደሯ፥ ሀገሪቱ ለቱርክ ባለሀብቶች ትክክለኛ መዳረሻ መሆኗን ነው የጠቆሙት፡፡

አምባሳደሯ የቱርክ ኩባንያዎች በተለያዩ ዘርፎች እውቀታቸውን እና ልምዳቸውን እያጋሩ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት፡፡

በኢትዮጵያ በ3 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር 187 የቱርክ ኩባንያዎች በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ተሰማርተው የሚገኙ ሲሆን፥ ከ30 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎችም የስራ እድል ፈጥረዋል፡፡

ምንጭ፦ አናዶሉ

You might also like
Comments
Loading...