Fana: At a Speed of Life!

በጎብኝዎች ቁጥር መጨመር ምክንያት የተዘጋው የባህር ዳርቻ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በታይላንድ ማያ ቤይ የተሰኘው የባህር ዳርቻ በጎብኝዎች ቁጥር መጨመር ምክንያት መዘጋቱ ተሰምቷል።

በታይላንድ ፔህ ፔህ  ሌህ ደሴት ውስጥ የሚገኘው ይህ  የባህር ዳርቻ ካለፈው ዓመት ጀምሮ በጊዜያዊነት ተዘግቶ ቆይቷል።

የባህር ዳርቻው በየጊዜው ስፍራውን የሚጎበኙ ጎብኝዎች ቁጥር ማሻቀቡን ተከትሎ በአካባቢው ስነ ምህዳር ላይ ከፍተኛ ጉዳት በመድረሱ ምክንያት መዘጋቱን የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል።

ማራኪ ገጽታ ያለውና በበርካቶች ተወዳጅ የሆነው የባህር ዳርቻ ከመዘጋቱ በፊት በቀን እስከ 5 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ይጎበኙት እንደነበር ተገልጿል።

በዚህም የውሃ ውስጥ አካላትን ጨምሮ በአካባቢው ስነ ምህዳር ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ነው የተነገረው።

ይህን ተከትሎም የሃገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት የስን ምህዳሩን ለማስተካከል በማሰብ የባህር ዳርቻውን ለጎብኝዎች ክፍት የሚያደርጉበትን ጊዜ ለተጨማሪ አመታት አራዝመውታል።

የባህር ዳርቻው በቅርቡ ይከፈታል ተበሎ ቢጠበቅም ለደህንነቱ በሚል እስከ ፈረንጆቹ 2021 ድረስ እንዲዘጋ ተወስኗል።

የባህር ዳርቻው በእነዚህ ጊዜያት ለጎብኝዎች ዝግ ከመሆኑም ባሻገር፥ አነስተኛ ጀልባዎች ከባህር ዳርቻው በብዙ ርቀት እንዲቀመጡና ዙሪያው ከሰው ንክኪ ነጻ እንዲሆንም ወስነዋል።

ማያ ቤይ በመልክዓ ምድር አቀማመጡ እና በውስጡ ባሉት የተለያዩ መዝናኛዎች ምክንያት ከመዝናኛነት ባለፈ ፊልሞችን ለመስራት አመች ቦታ መሆኑ ይነገራል።

በፈረንጆቹ 2000 ላይ ለዕይታ የቀረበውና አድናቆትን አትርፎ የነበረው ” ዘ ቢች” የተሰኘውና ሊዮናርዶ ዲ ካፕሪዮ የተወነበት ፊልምም በዚሁ ቦታ የተቀረፀ መሆኑ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like
Comments
Loading...