Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ በወቅታዊ ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ውይይት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 10፣ 2011(ኤፍ.ቢ.ሲ) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስተባባሪነት በወቅታዊ ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ውይይት ተደረገ።

ውይይቱ የተካሄደውም ቀደም ብሎ በፓርቲዎች መካከል በተደረሰው ስምምነት መሠረት መሆኑ ነው የተገለፀው።

የምክክር መድረኩ የመወያያ ርዕሶችም የኢትዮጵያ ፌዴራል ስርዓት ተቃርኖዎች፣ መንስኤዎችና ውጤቶች፣ የሰላም ምንነት፣ አስፈላጊነትና የባለድርሻዎች ሚና፣ የለውጡ ምንነት፣ አስፈላጊነት ፈተናዎችና፣ መፍትሔዎች እና በማህበራዊ ተሳትፎ ምንነት፣ አስፈላጊነትና መልኮቹ የሚሉ ናቸው።

በመድረኩ ዶክተር ሰሚር አሚን፣ ፕሮፌሰር ህዝቅያስ አሰፋ፣ ዶክተር ኤልሳቤጥ ሀይለ ጊዮርጊስ እና አቶ አንዷለም አራጌ የመነሻ ፅሁፍ ማቅረባቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like
Comments
Loading...