Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ጠ/ሚ አቶ ደመቀ መኮንን ከዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 5 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ጋር ተወያዩ።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ ወደ ዑጋንዳ አቅንቷል።

በውይይታቸውም በቀጠናዊ ትብብር እና በሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ መክረዋል።

ከዚህ ባለፈም በተለያዩ መስኮች ለረጅም ዓመታት የዘለቀው የኢትዮጵያ እና የዩጋንዳ የሁለትዮሽ ግንኙነትን የበለጠ ማጠናከር በሚቻልበት አግባብ ላይ መግባባት ደርሰዋል።

በተጨማሪም ሁለቱ ሃገራት በቀጣይ በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ትብብራቸውን ማሳደግ በሚችሉበት አግባብ ዙሪያ ተስማምተዋል።

ፕሬዚዳንት ሙሴቬኒም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተላከውን የትብብር መልዕክት ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እጅ መቀበላቸውን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 

You might also like
Comments
Loading...